ዜና

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላ/የተ/መ/ህ/ስ/ማህበር በ2011- 2012 በጀት ዓመት 42.9 ሚሊዮን ብር አተረፈ!!

መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም. (አዲስ አበባ፣ አዋጭ)

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር የጠቅላላ አባላት ተወካዮች ም/ቤት 14ተኛ መደበኛ ጉባኤ ከፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ የፋይናንስ ግብይት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ዱፌራ እና የህብረት ሥራ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳሬቦ ቡሴር በተገኙበት በራስ አምባ ሆቴል መስከረም 16/2013 ዓ.ም ተካሄደ፡፡ በጉባኤውም ላይ የህብረት ስራ ማኅበሩ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ሸለመ የህብረት ስራ ማኅበሩን ዓመታዊ (ከሐምሌ 2011 - ሰኔ 2012) ዝርዝር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች አቅርበዋል፡፡ በመቀጠልም በፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ኦዲት ባለሙያዎች አማካኝነት ከሰኔ 2011 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም የህብረት ስራ ማኅበሩን የአንድ ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴ ምርመራ ውጤት (የኦዲት ሪፖርት) በዝርዝር የቀረበ ሲሆን፤ በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት የህብረት ሥራ ማህበሩ ሀብት ወደ ብር 952.9 ሚሊዮን ማደጉን እና 42.9 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ኦዲተሮቹ ገልጸው ህብረት ሥራ ማህበሩ በአጠቃላይ የሂሳብ ፍሰቱ ጤናማ የሆነና እጅግ በጣም ጥሩ በሚባል የሥራ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ለጠቅላላ ጉባዔ ተወካዮች ገልፀዋል፡፡

የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች ም/ቤት አባላትም የህብረት ስራ ማኅበሩን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የኦዲት ሪፖርት ካዳመጡ በኋላ በሁሉም ዘርፍ የታየውን አመርቂ አፈጻጸም ከነበረው የኮሮና ወረርሽኝ ተግዳሮት አንፃር ከሚጠበቀው በላይ እንደሆነ በመግለጽ ህብረት ሥራ ማህበሩ ባተረፈው 42.9 ሚሊዮን ብር መሰረት የ2012 ዓ.ም. ዓመታዊ የትርፍ ክፍፍል በአንድ ዕጣ/ሼር 24% እንደሆነ በመወሰን አጠቃላይ ሪፖርቱን በሙሉ ድምፅ አጽድቀዋል፡፡

በተጨማሪም በአቶ ዘሪሁን ሸለመ የህብረት ስራ ማኅበሩ የ2013 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ ዕቅድ ቀርቧል፡፡ የጠቅላላ ጉባዔው ተወካዮችም በቀረበው ዓመታዊ ዕቅድ ላይ ከተወያዩ በኋላ እቅዱን በአንድ ድምፅ አጽድቀዋል፡፡

በመጨረሻም የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ተጋባዥ እንግዳ የፋይናንስ ግብይት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ዱፌራ አዋጭ በጥሩ ሁኔታ እያደገ ያለ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር መሆኑን ገልፀው ለዚህም አመራሩን ሰራተኛውን እና ምክር ቤቱን አመስግነዋል፡፡

የልገሣ መርሐ ግብሩ ማጠቃለያ ዝግጅት በስኬት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ (አዋጭ)፣ ግንቦት 28/2012 ዓ.ም

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር በሀገራችን በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ሲያደርግ የነበረውን የልገሣ መርሐ ግብር በስኬት አጠናቋል፡፡ በልገሣ ማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ አቶ ዑስማን ሱሩር የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር፣ የፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የአራዳ ክፍለ ከተማ ምክትል ሥራ አስፈጻሚና የክ/ከተማው ህዝብ ግንኙነት ወ/ሮ ህይወት ጉግሳ፣ የወረዳ 9 አመራሮች፣ የአዋጭ የገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማኅበር ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ገ/ሥላሴ፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራችን መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ሸለመ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው አርቲስቶችና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል፡፡ በዚህ ዝግጀት አቶ መስፍን ገብረ ሥላሴ የእለቱን የክብር እንግዳ አቶ ዑስማን ሥሩርን የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉ የጋበዙ ሲሆን አቶ ዑስማንም በንግግራቸው ”የሀገራችን ህብረት ሥራ ማህበራት የህዝቡን የልማት ፍላጎት ማሳካት የሚያስችሉ የመንግስት የልማት ውጥኖችን ወደ መላው ህብረተሰብ ማድረሻ ተቋማት ናቸው በማለት ከነዚህም ውስጥ አንዱና ውጤታማው የህብረት ሥራ ማህበር አዋጭ መሆኑን በመጥቀስ ለወገን ደራሽነታቸውን እያረጋገጡ ካሉ ህብረት ሥራ ማህበራት መካከልም አዋጭ አንዱ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ አዋጭ ይህንን የልገሳ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ለወገን ደራሽነቱን በተግባር ስላሳየን ለጠቅላላው አባላቱ በፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ስም ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ የአራዳ ክፍለ ከተማ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ እና የክ/ከተማው ህዝብ ግንኙነት ወ/ሮ ህይወት ጉግሳ በበኩላቸው አዋጭ እዚህ ወረዳ ላይ እንደመመሥረቱ ከዚህ

የድጋፍ መርሐ ግብሩ በመራዘሙ የአባላት ድጋፍ ተጠነክሮ ቀጥሏል

አዲስ አበባ (አዋጭ)፣ ግንቦት 10፣2012

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ችግር ውስጥ ለገቡ ወገኖች ለመድረስ እየተካሄደ ያለው የድጋፍ መርሐ ግብር በመራዘሙ ምክንያት የአባላት ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የድጋፍ መርሐ ግብሩ በዋናው ቢሮና በቅርንጫፍ ቢሮዎች እየተካሄደ ሲሆን አባላቱ የገንዘብ ፣ የደረቅ ምግብ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ፣ ሳሙና እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የድጋፍ መርሐ ግብሩ ልገሣ "የህብረት ክንዳችንን በማንሳት ለወገኖቻችን እንድረስ" በሚል መሪ ቃል እስከ ግንቦት 21/2012 ዓ.ም በሁሉም ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችንና በዋናው ቢሮ ይቀጥላል ፡፡ ለወገኖቻችን እንድንደርስ በጎ ምላሽ ለሰጣችሁን እያመሰገንን እርስዎም ማህበራዊ ኃላፊነትዎን እንዲወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን!!

የአዋጭ ምስክሮች

ሃገር አቀፍ ዜና

አዋጭ የቦንድ ግዢ ፈፀመ

አዋጭ የገ/ቁ/ብ/ኃላ/የተ/መሠ/የኅብረት ሥራ ማኅበር በሚያደርጋቸው ሀገራዊ እና ማኅበራዊ ተሳትፎዎች ውስጥ የሚመደበው የታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዢ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኅብረት ስራ ማኅበሩ ባለፉት አመታት በድምሩ የአንድ ሚሊዮን ሃምሳ ሺህ ብር ቦንድ መግዛቱ የሚታወስ ሲሆን በዚህ በጀት አመትም የተጀመረውን ሃገራዊ እንቅስቃሴ ለመደገፍ እና የተቀዛቀዘውን የቦንድ ግዢ እንዲነሳሳ አርዓያ ለመሆን በማሰብ የግማሽ ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዢ ፈፅሟል፡፡

የአዋጭ የምስክር ወረቀቶች እና ሽልማቶች

 

 

 

 

ቅርንጫፎች

ዋና መስሪያ ቤት (አዋሬ)
አጋር ህንፃ 2ኛ ፎቅ
ስልክ +251-11-557-97-98/57  
    +251-11-557-88-89/57 
    +251-11-557-98-99 
    +251-11-868-47-44
ኢሜል saccawach@gmail.com
ፖስታ ሳጥን ቁጥር 34752
ፌስ ቡክ ገፅ Awach SACCOS Ltd    

አዲስ አበባ

ቤልኤር ቅርንጫፍ
(አቤኔዘር ሕንፃ 2ተኛ ፎቅ) 
ስልክ +251-111-26-05-06
ስልክ +251-118-12-44-44/43/44

አራት ኪሎ ቅርንጫፍ
ስልክ  +251-111-56-49-92

ስድስት ኪሎ ቅርንጫፍ 
(ሊደርሽፕ ሕንፃ 3ተኛ ፎቅ)
 ስልክ +251-118-68-55-98

ስታዲዩም ቅርንጫፍ
(የሓ ሕንፃ 1ተኛ ፎቅ)
ስልክ+251-118-12-44-13

ልደታ ቅርንጫፍ 
(ኤ አይ ኤ ሕንፃ 2ተኛ ፎቅ)
ስልክ +251-118-68-55-97

ጀሞ ቅርንጫፍ
(ኤክስፕረስ ፕላዛ ሕንፃ 1ተኛ ፎቅ)
ስልክ +251-113-698-86-83

አዲሱ ገቢያ
(ጃምቦ ሕንፃ 3ተኛ ፎቅ) 
ስልክ+251-115-54-74-40

ሰዓሊተ-ምሕረት
(ድራር ሞል ሕንፃ 1ተኛ ፎቅ
ስልክ +251- 116-73-20-11

ክልል

ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ 
+251-118-12-42-42

ጫንጮ ቅርንጫፍ
+251-118-12-43-44