ስለ አዋጭ

ራዕይ

 በአገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂነት ያለው የገንዘብ ተቋም ፈጥሮ በኢኮኖሚ የዳበረ ሕብረተሰብ ማየት

 ተልዕኮ

ህብረተሰቡን በማስተባበር እውቀትንና ተገቢውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በፍላጎት ላይ የተመሰረተ አስተማማኝ የሆነ የፋይናንስ አቅርቦት ለአባላት እንዲኖር ማድረግ

ዓላማ

 • ዘላቂነት ያለው ገንዘብ ተቋም መፍጠር ባንክ ነክ አገልግሎት መስጠት
 • አባላት በማህበራቸው ገንዘብ እንዲቆጥቡ በማድረግ ኑሮአቸውን ማሻሻል
 • ለአባላት ፈጣን እና ምቹ በሆነ መንገድ በተገቢው ወለድ የብድር አገልግሎት መስጠት
 • ህብረተሰቡ የሚያገኘውን ገቢ በሥርዓት እንዲጠቀሙበት የቁጠባ ባህልን ትምህርት መስጠት
 •  ህብረተሰቡ ኋላ ቀር ከሆኑና ለብዝበዛ ከሚያጋጡ አራጣ አበዳሪዎች ማላቀቅ
 • ቁጠባ የሥልጣኔ መገለጫና የእድገት መሠረት መሆኑን ማሳወቅ
 • የአባላትን ቁጥር በመጨመር ለብድር አገልግሎት የሚውል የማህበሩን የገንዘብ አቅም ማሳደግ
 • በተለይ እገዛ የሚፈልጉ ሴቶችን በማበረታታት በገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ እንዲሰማሩ እና ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ ማበረታታት ማገዝ
 •  በአገራችን ኢትዮጵያ መንግሥት ባስቀመጠው የልማት ዕቅዶች የበኩላችንን አስተዋጽኦ በማድረግ ኃላፊነታችንን መወጣት
 • ለአባላት ተገቢውን ወለድ መክፈል
 •  ለማህበሩ የሚያስፈልጉ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ማፍራት ማስተዳደር
 •  ከተመሳሳይ ማህበራት ጋር ዩኒየን ወይም ፌዴሬሽን አባል መሆን ዕጣዎችን መግዛት ቁጠባዎችን መቆጠብ
 • ተከታታይ ሥልጠና ለአባላት፣ ለአመራር አባላት፣ ለቅጥር ሠራተኛ እና ለህብረተሰቡ መስጠት

የህብረት ስራ ማኅበራችን መርሆች

 • አባልነት ክፍት ሆኖ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ይሆናል
 •  የአባላት ዲሞክራሲያዊ ቁጥጥርና እኩል የአባላት ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ
 •  ከጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖ ነፃ ሆኖ ራስ ማስተዳደር
 •  ስለኅብረት ሥራ ማኅበራት ስልጠና ትምህርትና መረጃ ልውውጥ መኖር
 •  በኅብረት ሥራ ማኅበራ መካከል ትብብር ኅብረት መፍጠር
 •  በኅብረተሰቡ የማኅበራዊ ጉዳይ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ መሆን

 

ኅብረት ስራ ማህበራችን የሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት

ብረት ሥራ ማህበራችን ለአባላቱ የፋይናንስ ነክ እና ሌሎች የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል። እነሱም፡-

• የቁጠባ እና የብድር አገልግሎት፤

• የጊዜ ገደብ ተቀማጭ አገልግሎት፤

• አነስተኛ የብድር መድህን አገልግሎት፤

• የትምህርት ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት፤

• አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የግምጃ ቤት ሰነዶችና ቦንዶችን መግዛት፤

• አባላትን በማቀራረብ እርስ በእርስ የመረዳዳትና የመተሳሰብ ልምድ እንዲያዳብሩ ማድረግ፤

• የአባላትን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ከአቻ የኅብረት ሥራ ማህበራትና ከሌሎች አካላት ብድር በተመጣጣኝ ወለድ መበደር፤

• ሴቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ ተዘዋዋሪ ፈንዶችን እንዲሁም ብድሮችን በውል ስምምነት መሰረት ከተቋማት በመረከብ ማስተዳደር፣ ብድር መስጠትና ክትትል ማድረግ፤

• አባላት ያለባቸውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍና የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የማድረግ አገልግሎት መስጠት።