አባልነት

የኅብረት ስራ ማኅበራችን አባል ለመሆን የሚያበቁ መስፈርቶች

 • በሕግ መብቱ ያልተገፈፈ
 • ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው እና ከዚያ በላይ የሆነ ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች ከሆነ በህፃናት ቁጠባ
 • የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 1000፣ የዕጣ (ሼር) ሁለት እጣ ብር 2000 እና መደበኛ ቁጠባውን ብር 300 ወይም የደሞዙን 10% መቆጠብ የሚችል
  በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአራጣ አበዳሪ ያልሆነ
 • የማኅበሩን አላማና ደንብ የተቀበለና ግዴታውን ለመፈጸም ፈቃደኛ የሆነ
 • በማህበሩ የሥራ ክልል ውስጥ የሚኖርና ገቢ ያለው
 • የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ
 • ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ

አባል ለመሆን መሟላት የሚገባቸው፣

 1. የአባልነት መመዝገቢያ ክፍያ
 2. የመመዝገቢያ ክፍያ በአንድ ጊዜ የሚከፈል 1000 ብር ነው

 3. ዕጣ (ሼር)
 4. የአንድ ዕጣ (ሼር) መጠን ብር አንድ ሺ ሲሆን አንድ አባል ቢያንስ ሁለት እጣ ሁለት ሺህ ብር መግዛት አለበት

 5. መደበኛ ቁጠባ
 6. ማንኛውም አባል በወር ቢያንስ ሶስት መቶ አምሳ ብር መቆጠብ አለበት

 7. የፍላጎት ቁጠባ
 8. አንድ አባል ከመደበኛ ቁጠባ በተጨማሪ የፈለገውን/ችውን የገንዘብ መጠን በፍላጎት መቆጠብ ይችላል፡፡ የፍላጎት ቁጠባው አባሉ በፈለገው ጊዜ ወጪ ሊደርገው ይችላል፡፡