Error message

Deprecated function: The each() function is deprecated. This message will be suppressed on further calls in menu_set_active_trail() (line 2405 of /home/t40wi9z3tbcw/public_html/includes/menu.inc).

የህብረት ስራ ማህበራችን ገጽታ

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር አመሰራረትና እድገት

አዋጭ መቼ ተመሰረተ?

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ.የተ.የኅ.ሥራ ማህበር ህብረተሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ የተወሰነ ገንዘብ በመቆጠብ እራሱን በራሱ እነዲረዳና የቁጠባ ባህልን ለማዳበር እንዲሁም ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለአባላት ለመስጠትና የበኩላችንን በአገር ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ለውጥ ለማምጣት ታስቦ በ41 መሰራች አባላት አማካኝነት መጋቢት 1999ዓ.ም. ተመሰረተ፡፡ የተመሰረተውም የህብረት ስራ ማህበራትን ለማደራጀት በወጣው አዋጅ 147/91 እና በተሻሻለው 402/96 በአራዳ ክፍለ ከተማ ማህበራታ ማደራጃና ማስፋፊ ሲሆን ከመስከረም 2009ዓ.ም. ጀምሮ በፌዴራል ደረጃ በመመዝገብ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ላሉ ነዋሪዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

አዋጭ፡ በማንና እንዴት ተመሰረተ?

የማህበሩ መስራቾት 8 ወንድና 33 አነስተኛ ገቢ ባላቸው ሴት ሰራተኞች በድምሩ 41 አባላት ሲሆኑ ከነዚህ መስራቾች አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ዘሪሁን ሸለመ ማህበሩ እንዲመሰረት ያነሳሳቸውን ሲናገሩ “ተቀጥረው ይሰሩበት በነበረው መንግስታዊ ባልሆነው ድርጅት ያሉ ሰራተኞች በተለይ እሳቸው ኮኦርድኔት የሚያደርጉት በተለያየ ጊዜ ለትምህርት ፣ለቤት ዕቃ መግዣ፣ ለኮንዶሚኒየም ቤት ክፍያ፣ለቤት መስሪያ፣ ለሰርግ፣ ለተለያዩ ነገሮች ሰራተኞች ብድር ሲፈልጉ መስሪያ ቤቱ ለብድር የሚሆን ገንዘብ ስለሌለው ማግኘት አልቻሉም፤ ይህ ችግር ሲደጋገም ስለተመለከቱ የጋራን ችግር በጋራ ለመፍታት እንደሚቻል ሰራተኞቹን በማሳመን ለዚህም ደግሞ ገንዘብና ቁጠባ ማህበር ቢመሰርቱ መፍትሄ እንደሚሆን በማስረዳትና አደራጁንም አካል በመጥራት የአራዳ ክፈለ ከተማ ህብረት ስራ ማደራጃ ቢሮ ጋር በመሆን አቶ ዘሪሁን ሸለመ ማህበሩን በሊቀመንበርነት እንዲመሩ ሲወሰን እሳቸውም ካላቸው ኃላፊነት በተጨማሪ ማህበሩን በማደራጀትና አስፈላጊው ህጋዊ ነገሮች እንዲሟሉ ማህበሩ ህጋዊነት ካገኘም በኃላ ከመጋቢት 1999ዓ.ም. እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ በሊቀመንበርነት ሲመሩ የአባሉን ቁጥር ከ41 ወደ 2516 እንዲደርስ በማድረግ በየዓመቱ ኦዲት በማስደረግና ማህበሩ ምንም ዓይነት ጉድለት ሳይኖርበት ወጪን በመቀነስ ለማህበሩ ለስብሰባ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ስፖንሰር በማፈላለግ ማህበሩ አትራፊ እንዲሆን አድርገዋል፡፡

 

ከማህበሩ መስራች አባላት ጥቂቶቹ

በ2003 ዓ.ም. አቶ ዘሪሁን ሸለመ ከግብረ ሰናይ ድርጅቱ አመራርነት ለቀው ህብረት ስራ ማህበሩን በስራ አስኪያጅነት ለመምራት ሲወስኑ የማህበሩ አባላት ቁጥር 146 የነበረ ቢሆንም ማህበሩ በፊት ይሰሩበት ከነበረው መስሪያ ቤት በኮኦርድኔተርነት የሚከፍላቸውን ደሞዝ መክፈል ቀርቶ ግማሹን እንኳን መክፈል አልቻለም፤ ውሳኔ የሚፈልግ ነገር ገጠማቸው፣ አንድ ነገር ግን አሰቡ ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ቢሰሩ በጥቂት ጊዜ ማህበሩ እንደሚያድግና ከቀደመ ደሞዛቸው በላይ ወደፊት ሊከፍላቸው እንደሚችልና ከሁሉም በላይ ደግሞ ህዝብን በማገልገል የሚገኝ ደስታ እንደሚበልጥ አምነው ስራውን በሃላፊነት ለመስራት ከአመራሩ ተረከቡ፡፡

ማህበሩን ጥር 1 ቀን 2003ዓ.ም. በ146 አባላትና ከግማሽ ሚሊዮን ብር በታች በሆነ ካፒታል የተረከቡት አቶ ዘሪሁን ከስድስት ወር በኃላ ማህበሩ ኦዲት ሲደረግ የአባላቱን ቁጥር 300 በማድረስ እና የማህበሩን ካፒታል ወደ 1183294 (አንድ ሚኒዮን አንድ መቶ ሰማኒያ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና አራት) በማድረስ ከፍተኛ ስኬት አስመዝግበዋል፡፡ ይህው ስኬት በእጥፍ እንዲቀጥል ለ2004ዓ.ም. የታቀደ ቢሆንም በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ግን ከአራዳ ክፍለ ከተማ ማህበራት ማደራጃ ቢሮ ኦዲት ሪፖርት ማረጋገጥ እንደተቻለው ማህበሩ ከዕቅድ በላይ ሰርቶ የአባላቱን ቁጥር 622 እና የማህበሩን ሀብት ወደ 3391704 (ሶስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ሰባት መቶ አራት ብር ) ማድረስ ተችሏል፡፡

አባላቱንና ካፒታሉን ማሳደግ የማህበሩ የስኬት መጀመሪያ መሆኑን የሚያምነው አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስራ ማህበር በ2010ዓ.ም. መዝጊያ የአባላቱን ቁጥር 11,241 በማድረስ የማህበሩን ጠቅላላ ሀብት ደግሞ ወደ 216,886,116.41 አድርሷል፡፡ እነዚህን ተከታታይ ስኬቶችን በማየት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማህበራት ማደራጃ ዘርፍ እና ከአራዳ ክፍለ ከተማ ማህበራት ማደራጃ የስራ ሂደት ማህበራችን በከተማችንና በክፍለ ከተማችን ካሉ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ጋር ተወዳድሮ አንደኛ በመውጣት የሁለት ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በፌዴራል ህብረት ስራ ኤጀንሲም የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ከፍተኛ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬትም ተሰጥቶታል፡፡

የብድር ህይወት ኢንሹራንስ

ማህበራችን መጋቢት 13/2006 ዓ.ም. በጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነው መሰረት ከሀምሌ 1ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ተበዳሪዎች የሆኑ ሁሉ እንዲሁም ቀድመው ተበደሩ ከቀሪው ዕዳ ለወሰዱት ብድር 1% እንዲከፍሉ በማድረግ ብር 4,565,822.09  (አራት ሚሊየን አምስት መቶ ስልሳ አምስት ሺ ስምንት መቶ ሀያ ሁለት ብር ከ ዜሮ ዘጠኝ ሳንትቲም) መሰብሰብ ተችሏል ይህ ደግሞ ወደፊት በአባላት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ስጋት ያስቀራል፡፡

የሰው ኃይል

እስከ 2003 ዓ.ም. ድረስ ምንም ዓይነት የሰው ኃይል መቅጠር ያልቻለው አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስራ ማህበር በሶስት ፈቃደኛ አገልጋዮች ስራውን ሲያንቀሳቅስ ከቆየ በኃላ በ2003ዓ.ም ግን ለሶስት ሰራተኞች ተመጣጣኝ ባይሆንም ደሞዝ መክፈል ጀምሮሃል፡፡ በ2008 ዓ.ም. ያለውን የሰው ኃይል በማሳደግ አስራ አራት ባለሙያዎችን ይዞ ይገኛል፡፡ በሶስት ፈቃደኛ አገልጋዮች ስራውን ሲያንቀሳቅስ ከቆየ በኃላ በ2003ዓ.ም ግን ለሶስት ሰራተኞች ተመጣጣኝ ባይሆንም ደሞዝ መክፈል የጀመረው ማህበራችን በ2010 ዓ.ም. መዝጊያ ያለውን የሰው ኃይል በማሳደግ አርባ ሁለት ባለሙያዎችን ይዞ ይገኛል፡፡